Wednesday, 6 August 2014

የክርስቶስ ትምህርት




በኢዮስያስ ሽመልስ
 ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ   የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
                                                     1ዩሐ.1፥9
ምድር ላይ ኃያሌ በክርስትና ስም የሚንቀሳቀሱ የእምነት ተቋማት እንዳሉ ይታወቃል። ነገር ግን የቱንም ያህል በቁጥር ይበርክቱ እንጂ አንድ እውነተኛ መንገድ እንዳለች መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል።
በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። (ኤፌ.4፥4)
በመሆኑም እውነቱን ከውሸቱ ለመለየት እንዲቻለን የክርስትና ትምህርት የትኛው ነው? ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ማግኘት ይኖርብናል። ይህን ማድረግ ከተቻለን እውነት ወደምትመስል ሳይሆን ወደ እውነተኛይቱ መንገድ መመለስ እንችላለን።
          ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።(ምሳ.14፥12) ከዚህ እንደምንረዳው በሰው አስተሳሰብ እውነት የሚመስሉ ሁሉ መጨረሻቸው ሞት እንደሆነ ነው።

        የክርስትና ትምህርት የትኛው ነው?

  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በኖረበት ሰላሳ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር እውነተኛውን የክርስትና ትምህርት ለደቀመዛሙርቱ አስተምሯል። እንዲሁም በምኵራብ እና ህዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ማስተማሩን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።
ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ።(ማር.1፥21)
በመቀጠልም ለሰው ልጆች ነፍስ ሊከፍል ያለውን ዋጋ ከጨረሰ በኃላ የመዳንን ወንጌል ለሐዋርያት ሰጥቷል።ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።(ማር.16፥8)
ወንጌልን እንዲያስተምሩ ስልጣን ከተሰጣቸው  ሐዋርያት መካከል የመንግስተ ሰማይ ቁልፍ የተሰጠው ጴጥሮስ መዳን የሚገኝበትን መንገድ ሲያስተምር፦
ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።(ሐዋ.ሥራ 2፥38)
ቁ.41 ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤
ከላይ መረዳት እንደምንችለው በአንድ ቀን ሦስት ሺህ  ነፍስ ከኃጢያት እና ከሞት እስራት ሊፈቱ የቻሉበት ቁልፍ ንስሐ፥የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጥምቀት እና  የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ነው። ይህንን  መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመዳን አስተምህሮ የማይቀበል ማንኛውም ስመ ክርስቲያን መሳሳቱን አምኖ መመለስ ይኖርበታል። በተጨማሪ በሐዋ.ሥራ 11፥26 ክርስቲያን የሚለውን ስያሜ ያገኙት በቤተክርስቲያን ሲያስተምሩ የቆዩት ደቀመዝሙርት ነበሩ።
በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።(በሐዋ.ሥራ 11፥26)
ስለዚህ ማንም ሃይማኖተኛ እራሱን እና ተከታዮቹን ክርስቲያኖች ብሎ ቢጠራም የሐዋርያት ትምህርትን ከጣለ ኢየሱስን የጣለ በመሆኑ ምክኒያት አብ አይኖረውም ክርስቲያንም ሊባል አይችልም።
የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል።(ሉቃ.10፥16)
የእግዚአብሔርን መንግስት ከሚያስወርሰው ትክክለኛ መንገድ ውጪ  ሌላ አቋራጭ መንገድ የለም። መሰረቱም አንድ መሰረት የሐዋሪያት እና የነቢያት መሰረት ነው።
በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።(ኤፌ.2፥20)
አንዴ ከተመሰረተው መሰረት ውጪ መመስረት ዋጋው በእሳት መቃጠል መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።
ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።(1ቆሮ.3፥11)
በተለያዩ ዘመናት በሚነሱ ሐሰተኛ ነቢያት የፍልስፍና አስተምህሮ እንዳንስት ሐዋርያው ጳውሎስ ሲመክረን፦
እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።(ቆላ.2፥8) ይለናል።
ከሐዋርያት ትምህርት ውጪ ሌላው ልዮ ወንጌል እና የተረገመ  በመሆኑ ተከታዮቹን ሊያፀድቅ ከቶ አይቻለውም!!
እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።(ገላ.1፥8)


ማጠቃለያ
ሰዎች ሁሉ ይድኑ ዘንድ የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው።(1ጢሞ.2፥3-4) ስለዚህም ሰው ሁሉ ወደ እውነት እንዲመጣ ኢየሱስ ይታገሳል።
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።(2ጴጥ.3፥9)
     እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።እኔም የመለከቱን ድምፅ አድምጡ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ እነርሱ ግን፦ አናደምጥም አሉ።(ኤር.6፥16)
ዛሬ ይህንን ጽሑፍ የምናነብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዠ በመሆን ለነፍሳችን የዘላዓለም እረፍትን ለማግኘት እንድንችል ጌታ ኢየሱስ ይርዳን። አሜን!!!

3 comments:

  1. የዋሃንን ለመሸንገል::

    እንክርዳዱን ለማብቀል::
    የበግ ካባ ደርበህ::
    ባህሪህን ሰዉረህ::
    እስከ መቼ ሽንገላ?
    እስከ መቼስ ድለላ?

    ይበቃሃል መመሳሰል::
    እያደቡ መዘንጠል::
    ዘመነኛዉ ባለአደራ
    ለበጎቹ ባይራራ::
    የቀደሙት የጥንቶቹ::
    የቅዱሳን የአርበኞቹ::
    ይጥልሃል አጽማቸዉ::
    ስታቅራራ በርስታቸዉ።

    ReplyDelete
  2. ክርስቲያን የሚለውን ስም ተሸክመህ ስለምትኖር ጠላት ሁል ጊዜም ያሳድድሃል፡፡ አምላክህን በድፍረት የተቃወመች ይህች ዓለም አንተንም ሳትራራ ታንገላታሃለች፡፡ ልጆቿን ስትሾምና ስትሸልም በጊዜያዊ አዳራሽ በሚፈርሰው እልፍኝ ስታስቀምጣቸው አንተን በአፍአ ትወረውርሃለች፡፡ ይሄ ደግሞ ሊሆን ግድ ነውና በኃዘን ሳይሆን በደስታ ተቀበለው፡፡ ያንተ ክብር ያንተ ሽልማት ሩጫህን ስትፈጽም ነው፡፡ እየተሮጠ ዋንጫ የለም ፡፡ የመጨረሻውን ገመድ በጥሰህ ውድድሩን በድል መፈጸምህ ሳይረጋገጥ ክብር የለም፡፡ ስለዚህ ወዳጄ፤ አሁን ክብር ሽልማት አትጠብቅ፡፡ በመንገድ እንዳትቀር እየተጠነቀቅህ ሩጫህን በትዕግሥት ሩጥ፡፡

    ኢየሩሳሌም በሕፃናት እልቂት ታምሳለች፡፡ ሄሮድስ በቁጣ ሕፃናቱን ሊፈጅ ተነስቷል፡፡ስለሥልጣኑ ሲል ምንም የማያውቁትን የዋህ ሕጻናትም እየፈጀ ነው፡፡ ፍርድ ከጎደለበት ዳኛ ከጠፋበት ከዚህ አሳዛኝ ሥፍራ የአምላክ እናት ልጇን ታቅፋ ተሰደደች /ማቴ 2-13/፡፡ ዘንዶው ሊተናኰላት ሲነሣ እርሷ ከፊቱ ሸሸች /ራእ 12 4/።ግብፅ ጊዜያዊ መቆያ እንዲሆናት ተዘጋጅቷልና ወደዚያ አመራች፡፡ አንድ ጊዜ የሄሮድስ ወታደር፣ ሌላ ጊዜ ሽፍታ ከዚያም ሲቀጥል ኮቲባን የመሰለ ጨካኝ እያዘዘባት ተንገላታች፡፡ የአሸዋ ግለት፣ የፀሐዩ ሐሩር እየፈጃት ከሀገር ወደሀገር አቋርጣ ተጓዘች፡፡ እሞሙ ለሰማእታት /የሰማእታት እናታቸው/ ለልጆቿ ስደትን ልትባርክ በመከራ መካከል ሸሸች፡፡ በነፍሷም ሰይፍ አለፈ /ሉቃ 2-34/፡፡


    ያን ጊዜ ወላዲተ አምላክ ያነባችው ዕንባ መራራ ነው፡፡ለኃዘኗም መጠን አልነበረውም፡፡ ትንሽ ብላቴና ሕፃን ልጇን ይዛ ስትሰደድ ያየ የዚህችን ዓለም የክፋት መጠን ይረዳበታል፡፡ዓለም በመንገዷ ላልሄደ ሁሌም ጨካኝ ናት፡፡ያልተባበራትን አጥብቃ ትቃወማለች፡፡ ታሳድዳለች፡፡ ስለዚህም ድንግል ፈጣሪን ታቅፋ ተጠማች፡፡ጠላቶቿን በሰከንድ ማጥፋት የሚቻለው ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አብሯት ሆኖ በክፉዎች ስድብና ነቀፌታ ተንገላታች፡፡

    ወዳጄ ይህን ስደት በምታስብበት በዚህ ወቅት ላይ ሆነህ በአንተ የሚደርሰውን ፈተና እንደ በጎ ቁጠረው፡፡ፈተና ከየትኛው አቅጣጫ እንደሚመጣ አይታወቅም፡፡አንተ ባሰብከው ሳይሆን ጠላት ያዋጣኛል ባለው መንገድ ይፈትንሃል፡፡የሄሮድስን ገጸ ባሕርይ የሚላበስ ጨካኝና ስለሥልጣኑ ብቻ የሚያስብ ይልክብሃል፡፡ ለባለጊዜው የሚያደላ፣ ጊዜውን የሚመስል አጫፋሪም አይጠፋም፡፡ በምትጓዝበት በረሃ አንድ ጊዜ ቀማኛ፣ ሌላ ጊዜ ጦረኛ፣ ሲያሻው ደግሞ ምቀኛ ይልክብሃል፡፡ እነዚህ ሁሉ ገጸ ባሕርይ ተላብሰው የሚመጡ ናቸው፡፡እየተሠራ ያለውን ድራማ ልብ አንጠልጣይ የሚያደርጉ ተዋንያን ናቸው፡፡ አንተ በዚህ አትደነቅ፡፡ የሰውን ገጸ ባሕርይ ተላብሰህ ክፉዎችን መስለህ እንዳትተውን ብቻ ተጠንቀቅ፡፡ የድንግል ባሪያ የልጇ አገልጋይ መሆንህን ሳትረሳ በስደትህ ስደቷን አስብ፡፡ /ኢሳ 6-1/

    ታሪክ ራሱን ሲደግም ይኖራል፡፡ዓለም በክርስቲያኖች ላይ የምትሠራው የተንኮል ድራማ ይቀጥላል፡፡ አንዱ ድራማ ከሌላው የሚለየው ተዋንያኑ በመቀያየራቸውና ዓመታቱ በመፈራረቃቸው ነው፡፡ አንዳንዶች የሄሮድስን ገጸ ባሕርይ፣ የሐናና የቀያፋን ገጸ ባሕርይ ለመተወን ሰልፍ ይዘዋል፡፡ የክርስቶስን ሙሽራ ቅድስቲቱ ቤተ ክርስቲያንን ለማሳዘን ተነሥተዋል፡፡አንተ እርሱን ተውና የደጋጎችን ገጸ ባሕርይ ውሰድ፡፡ከማሳደድ መሰደድን ስለጊዜው ብለህ ለጥፋት ከመዳረግ የዘላለሙን ክብር ያዝ፡፡ስደት ያልፋል፣ሄሮድስ ያልፋል፣ረሃቡም ያልፋል፣ድራማው ሲያበቃ ሽልማቱ በደግነት፣በዓላማና በጽናት ለሮጡት ይሰጣል፡፡ስለዚህ ወዳጄ የምትተውንበትን ገጸ ባሕርይ መርጠህ በጥንቃቄ ተጓዝ፡፡

    ኦዝያን አለፈ እኔ ግን በዙፋኔ አለሁ የሚልበት አምላክህ በክብር የሚገለጥበት ቀን ቅርብ ነው/ኢሳ 6-1/።“ገሊላ ግቢ” ተብላ ነፍስህ የምትጠራበት ጊዜ ይኖራታል። እስከዚያው ስደትህን በደስታ ተቀበል። አስተውል! ሁል ጊዜ ዲዮቅልጣኖስ የለም፤ ቆስጠንጢኖስም ዕንባህን ሊያብስ ይገለጣል። ሁል ጊዜ ዐርብ የለም፤ ትንሣኤም ደግሞ ይመጣል።ያላመነው ይሄድና የሚያምነው ቦታ ይይዛል። ዓለም እንዲህ ናት፤ ስትታገልህ ትኖራለች። በመጨረሻ ግን እጇን ለፈጠራት ትሰጣለች። አይሁድ ያፍራሉ፣ መናፍቃን ስቀው ሳይጨርሱ ያለቅሳሉ። ወንበዴዎች የጅራፍ ድምጽ ይሰማሉ።ሁሉም የታገሉት የማይችሉትን መሆኑን ይረዳሉ። አንተ ብቻ በሃይማኖት ጽና።

    ከዓለም የሆኑት ስለዓለም ይናገሩ፣ዓለምን ይምሰሉ፣በጊዜያዊው ነገር ይጨነቁ፡፡አንተ ግን ከዓለም አይደለህም፡፡ የተዋሕዶ አርበኛ፣የድንግል የቃል ኪዳን ልጅ፣ የቅዱሳን ጸሎት በረከት ተካፋይ፣ መድኀኔዓለም በሞቱ የገዛህ ውድ ልጁ መሆንህን አስታውስ፡፡ሌሎች በቤተ ክርስቲያን አደባባይ የተወከሉበትን የዚህን ዓለም ነገር ይናገሩ፡፡ ስለሄሮድስ ታላቅነት ይመስክሩ፡፡አንተ ግን በየትኛውም ሥፍራ ክርስትናህን ግለጥ፡፡የተጠራህበትን ዓላማ ያዝ፡፡ እንዲህ የምታደርግ ከሆነ የስደትህን ምክንያት ስለምታውቅ መከራው ያንገዳግድህ ይሆናል እንጂ አይጥልህም፡፡ስደቱም ክብርህ ሊጨምር የመጣ መሆኑን ስለምታስብ እንድትጠነክር ያደርግሃል።አስተውል! ስደት ሁል ጊዜ ይኖራል፡፡ተሳዳጅ አሳጅም አሉ፡፡ሁሉም የቆሙለትን ዓላማ ይዘው እስከ ዓለም ፍጻሜ ይኖራሉ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. ""ከዓለም የሆኑት ስለዓለም ይናገሩ፣ዓለምን ይምሰሉ፣በጊዜያዊው ነገር ይጨነቁ፡፡አንተ ግን ከዓለም አይደለህም፡፡ የተዋሕዶ አርበኛ፣የድንግል የቃል ኪዳን ልጅ፣ የቅዱሳን ጸሎት በረከት ተካፋይ፣ መድኀኔዓለም በሞቱ የገዛህ ውድ ልጁ መሆንህን አስታውስ፡፡""yichin anbibehatal??????????????
      Eyosi ewunet yichin anbibehatal?????????????? ante gen embi alkew engdanm neger tekebelk!..........lemn???......mermr.......yekedemechitun.......menged teyik..felg.....kofr......tar.......tetatar.......dikem......lifa.........tenkeratet.......tengelata...........MIKNYATUM YEKEDEMECHITUN MENGED SITAGENG BERSUAM TEGUZEH KEFITSAMEWA SITIDERS E......R....E........F....T......N......TAGEGNALEH::(eyosi ayzoh berta gin chela atbel...........GOD FOLLOWS YOU......THANK YOU!!!!!!!!!!!

      Delete