በመጽሐፍ ያሉትን ፤ህግጋትን ሁሉ
አንዳች ሳታጓድል ሁሉ እንዲያሁ እንዳሉ፤
የምትጠብቅ ብትሆን አምላክን ‘ምትፈራ፤
ለምስኪኖች አዛኝ ልብህ የሚራራ፤
አምላክን አምላኪ ምጽዋት አድራጊ፤
ጸላይ ጸሎተኛ ሌት ተቀን ‘ማይተኛ፤
ብትሆን እንዲ ዓይነት ሰው፤
ስለ ጽድቅ የገባው፤
ይህ ሁሉ ልፋትህ መስዋዕነትህ፤
ፍሬ እንዲያፈራ አክሊል እንዲኖርህ፤
ከሚመጣው ቁጣ ነፍስህን ለማዳን፤
ከቅዱሳን ጋራ ባለሀገር ለመባል፤
መታሰቢያ ሳይሆን እንዲሆን ለመዳንህ፤
ነውርና ነቀፋ ተንኮል የሌለባት፤
በመንፈስ ቀድሶ በደሙ የዋጃት፤
እንዳትነቃነቅ በዓለት ላይ ያጸናት፤
አምላኳን ‘ምትመስል ለእርሱ የተዘጋጀች፤
የዚህን ዓለም ውጊያ በድል ያሸነፈች፤
አንድ
ታናሽ መንጋ እርስት የተሰጣት፤
በእርሷ
ውስጥ ለሚኖር ሰላም እረፍት ያላት፤
የቀደመች
መንገድ የሐዋርያት የነቢያት፤
ይህች
መሰረት መፈለግ መመርመር መያዝም አለባት።
ለሰው
ልጆች መዳን በአምላክ የተሰራች፤
በዚህች
ምድር ላይ ቤተክርስቲያናችን የኖህ መርከብ አለች።
No comments:
Post a Comment