ማንኛውም ክርስቲያን ነኝ የሚል አማኝ ሊክዳቸው የማይገቡ ሦስት እውነታዎች
1. አንድ ብቸኛ እግዚአብሔር አለ
ኢሳ.45፥5 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም ከእኔም በቀር አምላክ የለምበፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥
አንተ ግን አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።
ሚል.2፥10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?
ኤፌ.4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም
አባት አለ።
2. አንዱ እና ብቸኛው እግዚአብሔር በስጋ ተገለጠ
1ጢሞ.3፥16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
ዮሐ.1፥1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር
ነበረ።
ዮሐ.1፥14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ
ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።
3. ኢየሱስ አንዱ እና ብቸኛው እግዚአብሔር ነው
ማቴ.1፥23 እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታልየተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚልነው።ዮሐ.10፥31 አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራአሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው። አይሁድም። ስለመልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህነው እንጂ ብለው መለሱለት።ዮሐ.20፥28 ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።
(And Thomas answered and said unto him, My Lord and my God.)
No comments:
Post a Comment